በአሁኑ ጊዜ እየተሠሩ ያሉ HD ሪሲቨሮች የኢንተርኔት ኮኔክሽን ካለን: CCCam, IPTV, YOUTUBE, VOD, መጠቀም እንድንችል: እንዲሁም አዳዲስ የተለቀቁ KEYS ዳውንሎንድ ማድረግ እንድንችል ተደርጎ የተሰሩ ናቸው:: ታዲያ ይህን የኢንተርኔት ኮኔክሽን ለማግኘት 3G ወይም Wifi መጠቀም አለብን::
በ3G ኢንተርኔት ኮኔክሽን ለማግኘት: እንደየሪሲቨሮቹ የሚቀበሉት 3G dongle ይለያያል:: ለምሳሌ IBox 3030 ብንወስድ: ለ3G ኮኔክሽን የሚቀበለው ከብዙ በጥቂቱ በእነዚህ 3G dongle ነው::
Huawei E173
Vodafone K3765
Huawei E153
Vodafone K3770
Huawei E180/E180G
Huawei Vodafone K3773
Huawei E398
Huawei E303
Huawei E176
Wifi ኢንተርኔት ኮኔክሽን ካለን ደግሞ ይህን የኢንተርኔት ኮኔክሽ ለማግኘት ተጨማሪ አንድ ዕቃ ያስፈልጋል:: እሱም "USB Wifi Adapter" ይባላል (ፎቶ ይመልከቱ) እሱ አዳፕተር ካለን ሪሲቨራችን ላይ በመሰካት ሪሲቨራችን Wifi ኢንተርኔት ኮኔክሽን እንዲያገኝ ማድረግ እንችላለን::
ብዙ ጊዜ ቤታችን Wifi ኢንተርኔት ኮኔክሽን ላይኖረን ይችላል: ወይም ደግሞ ከሪሲቨራችን ጋር የሚስማማ 3G dongle ላይኖረን ይችላል:: ለእዚህ ቀላሉ መፍትሄ ላፕቶፕ ካለን: በላፕቶፓችን ላይ ኢንተርኔት ኮኔክችን ለማግኘት በምንሰካው 3G dongle አማካኝነት ተጠቅመን: ላፕቶፕላችን ላይ Virtual Wireless Hotspot ሶፍትዌር በመጫን: Wifi ኮኔክችን ፈጠርን ማለት ነው:: ከእዛም በእዛች ሪሲቨራችን ላይ በሰካናት USB Wifi Adapter አማካኝነት ሪሲቨራችን የኢንተርኔት ኮኔክሽን ማግኘት ይችላል::
የኢንተርኔት ኮኔክሽን ካገኘን: የተለያዩ ፊልሞችን: አዳዲስ ኪዎችን: ደግሞም የተዘጉ ቻናሎችን በCCCam አማካኝነት ማየት እንችላለን:: ከእዚህ በፊት የፃፍኩትን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሰዎች ትዝ እንደሚላችሁ: ለኢንተርኔት ኮኔክሽናችን ውድ የሚሆንብን IPTV, YOUTUBE, VOD መጠቀም እንጂ CCCam መጠቀም ብዙም የሚፈጅ አይደለም::
ደግሞም ቴሌ በከፍተኛ ሁኔታ በቅርብ ቀን የኢንተርኔት ታሪፍ እቀንሳለሁ ስላለ እንዳለው ከሆነ: ይህንን ነገር በሰፊው እንደጎረቤቶቻችን ኬንያ እንደምንጠቀም እርግጠኛ ነኝ::
ይህ ከላይ ያልኩሃችሁን በIBox 3030 በመጠቀም ራሴ ሞክሬ ያረጋገጥኩትን ነው:: ማስረጃውም ከታች ፎቶ በመመልከት ያረጋግጡ::
[img]
[You must be registered and logged in to see this image.][/img]
[img]
[You must be registered and logged in to see this image.][/img]