ሰላም ጤና ይስጥልኝ የፔጃችን ተከታታዮች ዛሬም የኳስ ቻናል ለማሰራት ምን ምን ያስፈልጋል በሚል ርዕስ ግልፅ የሆነ የተብራራ ፅሁፍ ይዘን ቀርበናል ካነበቡ በውሃላ ላይክ ማድረጎን እንዳይረሱ
# የኳስ ዲሽ ለማስገባት ስንት ሰሀን ያስፈልጋል?
ነፃ የኳስ ቻናሎች ለማየት ከ አንድ ዲሽ (ሰሀን) )በላይ ያስፈልገናል
# ለምን ሁለት ዲሽ አስፈለገን ?
#ሁለት ዱሽ ያስፈለገበት ምክንያት አብዛኛው ሰው 99% ያክሉ ናይል ሳት ይጠቀማል ናይል ሳት ላይ ደግሞ ሁሉም የሀገራችን ቻናሎች EBC 1, EBS, NAHOO TV, ሌሎች እና ኢንተርናሽናል የዜና ቻናሎች BBC ,CNN, Etc
ቻናሎች በናይል ሳት ስለሚገኙ ናይል ሳት ያለበት አቅጣጫ ደግሞ ከነፃ ኳስ ቻናሎች አቅጣጫ ጋር ተቃራኒ ነው ።
# ሁለት ዲሽ ያለንስ ምን ምን የኳስ ቻናሎች ይኖሩናል?
# እርሶ ሁለት ዲሽ ካሎት ይህን በሁለት መንገድ እንክፈለው አንዱ ባለ 90 ወይም ባለ 60 ቢኖሮት አንደኛው ግን ማለትም ኳሱን እንዲሰራበት የተባለው ሰሀን ባለ 180 cm ወይም ባለ 90 cm እንበልና
# ባለ 90 ሰሀን ላይ DUHOK፣NAGHA፣MAWAD፣HEWAD ፣ LAMAR የሚባለቱን ቻናሎች ያገኛሉ ማለት ነው እነዚህ ቻናሎች በሁለት lnb ሁለት ሳተላይት ላይ ነው ሚገኙት YEHASAT1A@52E እና NSS12@57E ማለት ነው
# ከላይ የየተቀሱት ቻናሎች ምን ምን ጫወታ ያሳያሉ?
# DUHOK ምርጥ ከሚባሉት ቻናሎች ውስጥ አንዱ ነው ይህ ቻናል በጥራት ቀዳሚ ሲሆን HD ቻናል ስለሆነ በ HD RECIVER ብቻ ነው ሚሰራው አረበኛ ኮሜንታተር ቢሆንም በጣም ጥራት ስላለው እና ማይቋረጥ ቻናል መሆኑ ተመራጭ ያረገዋል ሚያሳየቸው ጨዋታዎች እንግሊዝ ፕሪሜዬርሊግ ፣ሻምፒዮንስ ሊግ ፣ላሊጋ፣ሴሪያ፣ኢሮፖ ሊግ፣ሌሎችንምያሳያል ግን ሁሌም ለባርሴሎና እና ለ ማድሪድ ጨዋታ ቅድሚያ ይሰጣል ይህም ማለት አርሰናል ከ ቼልሲ ይጫወታሉ ባርሴሎና ከ ቫሌንሲያ ቢጫወቱ ጨዋታው እኩል ሳት ቢሆን ሚተላለፈው ጨዋታ የ ባርሴሎና ነው ማለት ግን የተለያዩ ሰአት ከሆነ ሁለቱንም ተከከታታይ ያሳያል ማለት ነው
# NAGHA፣MAWAD፣HEWAD ፣ LAMAR እነዚህ ቻናሎች ደሞ ዋነኛ ደስ ሚሉት በሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ላይ ነው እኩል ሰአት ላይ ሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎችን በተለያዩ ሁለት ቻናሎች ሁለቱንም ጨዋታ ያሳያሉ በተጨማሪ ላሊጋ ያሳያሉ የባርሳ እና የማድሪድ ጨወታዎችን እንደዚሁም ምሽት ከ 2 ሰአት በውሃላ ሚደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሜዬርሊግ ጨዋታዎች ያሳያሉ ዋነኛ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ላሊጋ በትክክል ያሳታሉ በማንኛውም ሪሲቨር ይሰራሉ SD & FREE ናቸው ማለት በዚህ አጋጣሚ እዚው ሳተላይት ላይ ምርጥ የፊልም እና የሙዚቃ ቻናሎች እንዳሉ ላስታውሳቹ
ሌላኛው ቻናል PTV SPORT & PTV BATIONAL ሲሆኑ አንድ ትልቁ ሰሀን ካላቹ ነው እነዚህን ቻናሎች እና ከላይ ፅፌ የነበሩትን ቻናሎች በአንድ ዲሽ ማግኘት ሚችሉት
# PTV SPORT & PTV BATIONAL ካሎት እንግሊዝ ፕሪሜዬር ሊግ እና ቦንደንደስ ሊጋ ያሳያሉ ፕሪሜዬርሊግ ምንም ጨዋታ አያመልጦትም ማለት ይቻላል እኩል ሰአት ላይ አልፍ አልፎ ሁለት ጨዋታዎችን በሁለት ቻናል ያሳያሉ ደስ የሚል እንግሊዘኛ ኮሜንታተር ነው ምርጥ የሚባል ጥራት አለው ልብ በሉ ይህ ቻናል ሚሰራው በ ትልቁ ዲሽ እና በ C BAND LNB ብቻ ነው
# ግልፅ አድርገን ያቀረብነው ይመሰለኛል ዋናው ነገር ሁለት ዲሽ ይኑሮት ናይል ሳት አልፈልግም ካሉም አንድ ዲሽ በቂ ነው ጥያቄ አስተያየት ካላቹ ኮሜንት ያድርጉ
ላይክ ማድረጎን እንዳይረሱ ላይክ ሲሉም ነው ሞራል ሁኖን ጥሩ ፣ ግልፅ እና እውነተኛ መረጃ ምናቀርብሎት
በተጨማሪ በፌስቡክ አዲሬሴ ከፔጄ ተጨማሪ chat ላይ ጥያቄ ካሎት ይህ ነው አድራሻዬ https://m.facebook.com/samsonsisy
እንደዚሁም የዲሽ መስራት መማር ከፈለጉ ይህ ዌብሳት የኛ ነው ይጎብኙልን
https://samidish.forumotion.com/ማንኛውንም የዲሽ ስራ ማሰራት ከፈለጉ ደውለው ያማክሩን