የተበላሸ የሱፐርማክስ ሪሲቨርን በሃይፐርተርሚናል ማስተካከል
ሪሲቨሩ አፕግሬድ እያደረገ እያለ መብራት ቢጠፋ ወይም የተሳሳተ ሶፍትዌር ቢጫንበት አልነሳ ይላል፡፡
ታድያ ይህን ለማስተካከል ሎደር ፕሮግራም ኮምፒዩተራችን ላይ በመጫን እና RS232 ኬብል በመጠቀም
ትክክለኛውን ሶፍትዌር/ፈርምዌር ስንጭንበት ይስተካከላል፡፡ ምናልባት ለፈለግነው ሞዴል የሚሆን ሎደር ፕሮግራም
ማግኘት ካቃትን፣ የሲሪያል ኮሙኒኬሽን ሰፖርት ማድረግ የሚችሉ ፕሮግራሞችን(እንደ ሃይፐርተርሚናል እና ፑቲ አይነቶችን)
መጠቀም እንችላለን፡፡
በዚህ ጽሁፍ ሃይፐርተርሚናልን እንዴት ለሱፐርማክስ ሪሲቨሮች እንደሎደር መጠቀም እንደምንችል አስረዳለሁ፡፡
ዊንዶውስ xp ላይ programs->Accessories->communications->hyperterminal
በማለት መክፈት ይቻላል፡፡ ከxp በኋላ ያሉት ላይ ደግሞ ዊንዶውስ ፊቸር ኦን ኤንድ ኦፍ የሚለው ዉስጥ
ገብተን ኦን ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ በከፊሎች ደግሞ አብሮ ከዊንዶውስ ጋር ኢንስቶል ሆኖ ላይሆን ይችላል፡፡
ያሲሆን ደግሞ ከxp pc ላይ ሃይፐርተርሚናል እና dll ፋይሉን በአንድ ፎልደር ኮፒ አድርገን ካመጣነው
ይበቃናል፡፡ ወይም ከዚህ ዉስጥ ዳዉንሎድ ማድረግ እንችላለን፡፡
ከዚህ በመቀጠል የሚከተሉትን በቅደም ተከተል እናደርጋለን
1.ሪሲቨሩን ከኮምፒዩተራችን ጋር RS232 ኬብል እናጋናኛለን
2.ሃይፐርተርሚናሉን ካስነሳን በኋላ የሚከተሉትን ሴትንግ እናስተካክላልን
file>properties የሚለው ዉስጥ Connect using በሚለው ቦታ የሲርያል ፖርቱን ቁጥር
እናስገባለን፣ COM1, COM2 የሚባለውን ማለት ነው፡፡
file>properties>configure የሚለው ጋር ደግሞ
Bit rate: 115200
Data bit: 8
Parity: None
Stop Bit: 1
Flow control: None
ከላይ ያሉትን ካስገባን በኋላ አፕላይ ብለን ኦኬ እንለዋለን፡፡
3.ትክክለኛ ሶፍትዌር ፋይሉን አታች እናደርጋለን፣
ይህን ለማድረግ Transfer>sendFile ብለን ከሚመጣው ዊንዶ ላይ Filename በሚለው ቦታ
ላይ ብሮውዝ ብለን ሶፍትዌሩን እናስገባልን፡፡ Protocol በሚለው ላይ ደግሞ Ymodem የሚለውን እንመርጣለን፡፡
4.ከሪሲቨራችን ፊትለፊት ያለውን Volume up የሚለውን key በአንድ እጃችን ተጭነን ይዘን
በሌላ እጃችን ሪሲቨሩን እናበራዋልን፡፡ ይህን ማድረግ ሪሲቨሩ በRS232 የሚመጣውን ዳታ እንዲያዳምጥ ትእዛዝ
ይሰጠዋል፡፡ የሃይፐር ተርሚናሉ ዊንዶ ላይ 'ccc' የሚል ጽሁፍ ይመጣል፡፡ ያም ማለት ሪሲቨራችን ይሚላክለትን
ለመቀበል ዝግጅ ነው ማለት ነው፡፡
5.አሁን እላይ በተራ ቁጥር አምስት ላይ ያዘጋጀነውን send እንላለን፡፡
6. በኮምፒዩተራችን ላይ ያለውን ፕሮግረስ ባር 100 ፐርሰንት እስኪደርስ በትግስት እንጠብቃለን፡፡
7. ፋይሉ ትራንስፈር አድርጎ ጨረሰ ማለት ግን አፕዴቱ አለቀ ማለት አይደለም፡፡
ሪሲቨሩ የተቀበለውን ፋይል ከRAM ወደ ፍላሽ ኢንስቶል ለማድረግ ሌላ ተጨማሪ ጊዜን
ይፈልጋል ስለዚህ አሁንም በትግስት እስኪጨርስ እንጠብቃለን፡፡ ሪሲቨሩ ራሱ ሪስታርት ያደርጋል፣
ያኔ ጨረሰ ማለት ነው፡፡ አሁን ሪሲቨራችን ተስተካክሏል፣ ለስራ ዝግጁ ነው፡፡
ይህ መረጃ ከጠቀሞት አስተያየቶን ከስር በማስፈር እና በስተቀኝ በኩል ያለውን የፕላስ ምልክት ጫን ማድርግ
እንዳይረሱ፡፡ በጽሁፉ ዉስጥ ግልጽ ያልሆነ ወይም ሊታረም የሚገባው ጉዳይ ካዩም ከስር መልክት ቢተው እንዲታረም
ይደረጋል፡፡
መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡