- kirubel tofik wrote:
- be Eurostar Eb9700Gold+ lay lela software benenchen weyeme lesu yemayehon benechen ena upgread benadereg mene yefeteral?
የሚፈጠረው ነገር እንደሁኔታው ይለያያል፡፡
ሎደር ሶፍትዌሩን ከሆነ በተሳሳተ መልኩ አፕግሬድ የሆነው፣ ኢፕሮሙ ተነቅሎ ላዩ ላይ ትክክላኛው ሎደር ኮፒ መደረግ ይኖርበታል፡፡ በተሳሳተ መልኩ አፕዴት ያልከው ሜይን ሶፍትዌሩን ከሆነ ሪሲቨርህ አልነሳ ይላል፣ ይህንን ችግር ደግሞ ትክክለኛዉን ሶፍትዌር ስትጭንበት ይስተካከላል፡፡ በተሳሳተ መልኩ አፕዴት ያልከው ዳታዉን ከሆነ፤ ዳምፕ አድርገህ የነበረውን ስትጭንበት ይስተካከላል፡፡ እንግዲህ ከሞላ ጎደል ሊፈጠር የሚችለው እና መፍትሄዎቻቸው እነዚህ ናቸው፡፡ በተረፈ ጥያዌው ሃይፖተቲካል ስለሆነ ቁርጥ ያለ መልስ ለመስጠት እንዲያመች ከተጨባጭ መረጃ ጋር ቢሆን ይመረጣል፡፡
በመጨረሻም፣ የቶፒኩ አርዕስት ላይ ሙሉ ጥያቄው አይጻፍም፡፡ አርዕስት አጠር ተደርጎ ነው የሚጻፈው፤ ከዛ ዉስጡ ጥያቄህን አብራርተህ ትጽፈዋለህ፡፡ ቶፒኩንም ተዣማጅ በሆነበት ቦታ ብትፈጥረው ጥሩ ይሆናል፡፡ ለዛሬ ይህን መልስ ካነበብክ በኋላ አሁን ካለበት ኢንክሪፕሽን/ዲክሪፕሽን ወጥቶ ወደሚቀርበው ቦታ እንዲሄድ ይደረጋል፡፡
መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡[/color][/size]