| Card sharing, Server, IPTV, Internet TV | |
|
+18Gadissa biruk man123 onewow adisu yohanes Girma Zewdie yosef99 kibrulaw yordiyo hageregenet Kaleab470 dani.yohannes fiker tamiratta tadiwos.y mekaddisu satdish abera Admin 22 posters |
|
Author | Message |
---|
Admin Admin
Posts : 725 Points : 1175 Reputation : 303 Join date : 2014-09-01
| Subject: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Mon Oct 13, 2014 10:27 am | |
| Card sharing, Server, IPTV, Internet TV
ስለዲሽ ፍቅር ካልዎት ስለእነዚህ ነገሮች ሳይሰሙ አይቀርም አዎ በእኛ ሀገር ስላልተጀመረ እንጂ በሌሎች ሃገሮች አፍሪካንም ጨምሮ እየተለመደ የመጣ አሁን እኛ እየተጠቀምን ያለውን በጣም ሁላቀር የሚያረግ ሲስተም ነው:: ከላይ በአርዕስት ያስቀመጥኩዋቸውን እንደተለመደው ቴክኒካል ነገሩን ትተን ለእኛ መረዳት በሚጠቅም ሁኔታ ለማስቀመጥ ልሞክር:: Card sharing (Internet Key Sharing) (IKS)ይህን ሲስተም ከቃሉ ለመረዳት እንደምንችለው በክፍያ የሚታዩ የሳተላይት ቲቪ ቻናሎችን አንዱ ሰው ሕጋዊ የሆነ ካርድ ገዝቶ ለእራሱ ብቻ ከመጠቀም ሌሎች ሕጋዊ ካርድ ለሌላቸው እንዲጠቀሙበት ማጋራት ማለት ነው:: እንዴት ነው ማጋራት የሚቻለው??ይህ ሕጋዊ ካርድ ያለው ሰው እሱ ስክራምብልድ የሆኑ ቻናሎችን ለማየት ካርዱን ሪሲቨሩ ውስጥ ሲከት: ያ ካርድ በተሰራበት ሲስተም አማካኝነት ስክራምብልድ ቻናሉን ለመክፈት የሚያስፈልገውን ኮድ ይለቃል:: ይህ ከካርዱ የወጣውን ኮድ ሪሲቨሩን ከኮምፒተር ጋር በማገናኘት ኮምፒተሩ ላይ ባለው ኢምዩሌተር ሶፍትዌር ወይም ደግሞ ሊኑክስ ቤዝድ (Linux based) የሆኑ ሪሲቨሮች ከሆኑ (በእኛ ሃገር እንደ IBox, Starsat, Strong, አንዳንድ ጥቂት የSupermax ሪሲቨር አይነቶች) በቀጥታ ሪሲቨሩ ላይ ባለው ሰርቨር አማካኝነት ከስማርት ካርዱ የሚገኘውን አስፈላጊ ኪ ዳታን ለሌሎች ያጋራል:: በእዚህም መንገድ አንድ ሕጋዊ ካርድ ያለው ሰው ሕጋዊ ካርድ ለሌላቸው ከ1000 በላይ ሰዎች ሼር ማረግ ይችላል:: Serverየእዚህ ካርድ ሼሪንግ እየተስፋፋ ሲመጣ ሰዎች እንደግሩፕ አይነት አቋቁመው: በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ ሰዎች: ነገር ግን ተመሳሳይ ሳተላይቶችን የሚያገኙ: አንዱ ያለውን የአንድ ካምፓኒ ካርድ ለሌሎች ሼር ሲያደርግ: ሌላው ደግሞ የሌላን ካምፓኒ ካርድ እንዲሁ ሼር እያደረገ: ይህንን አንድ ቦታ አንድ ላይ አድርገው ሼር የሚያደርጉበት አንድ ሃርድዌር (ዕቃ) ይጠቀማሉ:: ያ የሚጠቀሙት ሃርድዌር ሰርቨር (Server) ይባላል:: ያ ሰርቨር 24ሰዓት ከኢንተርኔት ጋር የተገናኘ ስለሆነ: ከእዛ ሰርቨር ጋር በኢንተርኔት የተገናኘ ሰው ሁሉ መጠቀም ይችላል:: ያላቸውን ሕጋዊ ካርድ ሼር ሳያደርጉ ዝም ብለው ሰዎች በነፃ እንዳይጠቀሙ ሰርቨሩን በፓስወርድ ይዘጉታል:: ከሰርቨሩ ለመጠቀም ሰዎች ሬጂስተርድ መሆን አለባቸው:: እንዲሁም አነስተኛም ቢሆን የተወሰነ ክፍያ ለተወሰነ ጊዜ ይከፍላሉ:: ነገር ግን ዋናው ጥቅሙ ምንድነው የሚከፈለው ክፍያ ለዋናው ካርድ ከሚከፈለው ጋር ሲወዳደር በጣም የቀነሰ መሆኑና ከእዛም ባለፈ የተለያዩ ካምፓኒዎችን ካርዶች ምንም እንኳ እያንዳንዳችን ካርዱም ባይኖረንም ለመጠቀም መቻላችን ነው:: የኢንተርኔት ኮኔክሽን ያስፈለገበት ምክንያት የኪዎቹን ዳታ ለማግኘት ብቻ ስለሆነ የምንጠቀምበት: ለኢንተርኔት ኮኔክሽን የምንከፍለው ዋጋ በጣም አነስተኛ ነው:: ቻናሎችን ለማየት የግድ መጀመርያ በዲሻችን አማካኝነት ቻናሎች መምጣት አለባቸው:: እስካሁን በሚታወቀው ከ18 በላይ ትላልቅ ሰርቨሮች ሲኖሩ አንዲሁም ከ5000 በላይ HD የሆኑ በክፍያ የሚታዩ ቻናሎች ባጠቃላይ በአለም ላይ ካሉ ከ90% በላይ የከፍያ ቻናሎች በእዚህ ሲስተም ይታያሉ:: ስለዚህ ወደፊት የምገዛቸው ሪሲቨሮች በእራሳቸው ኢንተርኔት ኮኔክሽን ለማድረግ አማራጭ ያላቸውና በውስጣቸው server option ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል:: IPTV IPTV (Internet Protocol Television) ይህ ሲስተም ለመጠቀም መጀመርያ ሪሲቨራችን ይህ ሲስተም ሊኖረው ይገባል:: በሃገራችን ይህ ሲስተም ያላቸው ሪሲቨሮች IBox, Starsat, Strong እና አንዳንድ ጥቂት የSupermax ሪሲቨር አይነቶች ናቸው:: ይህ IPTV ከCard sharing የሚለየው ነገር መጀመርያ እንደካርድ ሼሪንግ: ሼር የሚደረግ ኪ ዳታ አይደለም:: ሪሲቨራችንን በWIFI ወይም በ3G ኢንተርኔት ኮኔክትድ ከሆነ በሁዋላ: ይህን ሰርቪስ በሚሰጡ ካምፓኒዎች አማካኝነት የተለያዩ የነፃና በክፍያ የሚታዩ ቻናሎችን በአነስተኛ ክፍያ የምናይበት ነው:: የእዚህ ሲስተም ትልቁ ጥቅም የምንፈልገው ቻናል እኛ ሀገር ይደርሳል አይደርስም የሚባል ነገር የለውም:: የትኛው ሃገር የሚተላለፍ ቻናል በIPTVማየት አንችላለን:: ምክንያቱም ካምፓኒዎቹ በምርጫችን ስለሚሰጡን:: የቲቪ ቻናሎችን ብቻ ሳይሆን ቪድዮችንም እንደምርጫችን ማየት እንችላለን:: ይህን ጥቅም ከCard sharing አናገኘውም:: ምክንያቱ በCard sharing ቻናሎቹን የምናገኘው ጣራ ላይ በሰቀልነው የዲሽ ሰሃን ሲሆን: በIPTV ግን ቻናሎቹን የምናገኘው ይህንን አገልግሎት ከሚሰጡ ካምፓኒዎች በአነስተኛ ክፍያ ከምንገዛው ፓኬጅ ነው:: የእዚህ IPTVሲስተም ጉዳቱ: ቻናሎቹ ወደሪሲቨራችን የሚመጡት ጣራ ላይ በሰቀልነው ዲሽ አማካኝነት ሳይሆን በኢንተርኔት ስለሆነ: ዋጋው ትንሽ ሲወደድ: በእዛ ላይ በጣም ሃይ ስፒድ የሆነ ኢንተርኔት ኮኔክሽን ይፈልጋል:: ስለዚህ ለእኛ ከIPTV ይልቅ Card sharing ይመረጣል:: ምክንያቱም በCard sharing በየተወሰነ ሰከንዶች የምንቀበለው ኪ ዳታ የሆነ በጣም አነስተኛ የሆነ ባይትስ ስለሆነ:: ነገር ግን ኢንተርኔታችን ፍጥነትና አስተማማኝነት ሲሻሻል እና ዋጋው ሲረክስ ደግሞ ያኔ ከCard sharing ይልቅ IPTV ይመረጣል:: Internet TV (Web TV)ይህን አገልግሎት ለመጠቀም መጀመርያ ቴሌቭዢናችን ዲጂታል መሆን ሲኖርበት: ከእዛም ቀጥሎ በቀጥታ ቴሌቭዢናችንን ከአኢንተርኔት ጋር በማገናኘት የተለያዩ የቲቪ ቻናሎችን የምናይበት ነው:: በእዚህ ሲስተም ሪሲቨር ዲሽ የሚባል ነገር የለም:: IPTVዲሽ ሰሃን ባይፈልግም: Internet TV ግን ሙሉ ለሙሉ ዲሽ ሰሃንም ሪሲቨርም አይፈልግም:: ከላይ ለ IPTV እንደገለፅኩትም ሃይ ስፒድ እና አስተማማኝ ኢንተርኔት ኮኔክሽ ይፈልጋል:: እንግዲህ ከላይ ከሃገራችን ውጪ ያሉ የዲሽ ተጠቃሚዎች የደረሱበትን እና እየተጠቀሙ ያሉትን ነግሪያችሁዋለሁ:: በእዚህም የዲሽ አጠቃቀም ምን ያህል ወደሁዋላ እንደቀረን ሳትረዱ አትቀሩም:: ነገርግን የኢንተርኔት ኮኔክሽናችን ሲስተካከል በአንዴ ልንጀምረው የምንችለው ነገር ነው:: እንግዲህ ተጠቃሚዎች እንዲህ ከተጠቀሙ የቴሌቭዢን ካምፓኒዎቹ ደግሞ ገቢያቸው እንደሚቀንስ ጥርጥር የለውም:: ስለዚህ አርፈው እንደማይቀመጡ ለማንም ግልፅ ነው:: በቴሌቭዢን ካምፓኒዎቹ በኩል ይህን ችግር ለመፍታት መጀመርያ የሄዱበት መንገድ ሕጋዊ መንገድ ነው:: ሰርቨር አደራጅተው በአነስተኛ ክፍያ ለሰዎች ሼር የሚያረጉትን አሳዶ መያዝና ማስቆም ነው:: ይህም ቢሆን ባለሰርቨሮቹ የተለያዩ ቴክኒኮችን በመጠቀም አድራሻቸው እንዳይገኝ አርገዋል:: ስለዚህ የቴሌቭዢን ካምፓኒዎች ሌላ ዘዴ እንዲፈልጉ አስገድድዋቸዋል:: ይህም ዘዴ Pairing system ይባላል:: Pairing system ይህ ሲስተም የሚጠቀምበትን መንገድ በቀላሉ ለማስረዳት የBein Sport ካርድን ለምሳሌ መጠቀም ጥሩ ነው:: ሰዎች በካርድ ሼሪንግ አንዱ የገዛውን ሕጋዊ ካርድ ለእርሱ ቅናሽ ዋጋ በመክፈል የእሱን ካርድ ሼር በማድረግ በኢንተርኔት በየቤታቸው በአንዱ ካርድ አማካኝነት ከአንድ ሺ ሰዎች በላይ ይጠቀሙ ነበር:: ካምፓኒው ይህ ገቢውን ስለቀነሰበት ከ ማርች 01, 2014 ጀምሮ ካምፓኒው በመረጣቸው ሪሲቨሮች ብቻ ሰዎች እንዲጠቀሙ በማረግ (ያኔ ሰዎች ይጠቀሙ የነበረው HUMAX HD-FREE እና HUMAX IR 3000 ነበር) የእነዚህንም ሪሲቨሮች ሲርያል ቁጥር (Serial numbers) ከካርዱ ጋር አብሮ በመመዝገብ: ሪሲቨሩ ኪዳታውን ከማንበብ ይልቅ ከካርዱ ጋር የተያያዘውን ሲርያል ነበሩን እንዲያነብና: ከእራሱ ከሪሲቨሩ ሲርያል ቁጥር ጋር ካልተስማማ ማንበብ እንዳይችል በማድረግ: ሰዎች ካርድ ሼር እንዳያደርጉ ለማድረግ ችለዋል ከእዛም ባለፈ ለBein Sport ካርድ ብቻ መጠቀም የሚያስችሉ የእራሳቸውን የተለያዩ ሪሲቨሮችን ይህንን ችግራቸውን ለመፍታት አቅርበዋል:: ይህ ብቻ ሳይሆን ሌላም ዘዴዎችን ይጠቀማሊ… የኪ ቢትሱን በማብዛት… ቶሎ ቶሎ ኪ ኮዶቹን በመለዋወጥ… ይህ ሁሉ ይደረግ እንጂ ሰዎች የቴሌቪዢን ካምፓኒዎች ለሚፈጥሩዋቸው ነገሮች ሁሉ የተለያዩ ነገሮችን በመፍጠር እነዚህን ቻናሎች ከማየት አልቦዘኑም:: ይህ ፅሁፍ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት "Thank you" ማለትን አትርሱ:: አስተያየት ካሎትም comment ያድርጉ:: [img] [You must be registered and logged in to see this image.][/img]
Last edited by kstar on Tue Jul 14, 2015 3:07 pm; edited 5 times in total (Reason for editing : Navigation) | |
|
| |
abera Junior member
Posts : 10 Points : 16 Reputation : 2 Join date : 2014-10-01
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Mon Oct 13, 2014 10:54 am | |
| I found this piece of writing as informative and descriptive as well. pls keep it up. | |
|
| |
abera Junior member
Posts : 10 Points : 16 Reputation : 2 Join date : 2014-10-01
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Mon Oct 13, 2014 10:56 am | |
| | |
|
| |
satdish
Posts : 8 Points : 16 Reputation : 2 Join date : 2014-09-02 Age : 38
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Mon Oct 13, 2014 9:08 pm | |
| | |
|
| |
mekaddisu
Posts : 9 Points : 13 Reputation : 0 Join date : 2014-12-25
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Thu Jan 01, 2015 12:27 am | |
| Very informative, clear and concise. Thank you! | |
|
| |
tadiwos.y
Posts : 7 Points : 7 Reputation : 0 Join date : 2014-11-29
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Sat Jan 24, 2015 4:13 pm | |
| I Loved IT. Thank you V.much. | |
|
| |
tamiratta Member
Posts : 92 Points : 133 Reputation : 37 Join date : 2014-10-03
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Mon Jan 26, 2015 11:15 am | |
| This is a marvelous piece of info thanks Admin! | |
|
| |
fiker
Posts : 8 Points : 9 Reputation : 1 Join date : 2014-11-20
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Sat Jan 31, 2015 1:30 pm | |
| thanks vvvvvvvvvvvvvvvery much ? but i ask u one question? this card sharing working for dstv? | |
|
| |
Admin Admin
Posts : 725 Points : 1175 Reputation : 303 Join date : 2014-09-01
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Mon Feb 02, 2015 10:49 am | |
| - fiker wrote:
- thanks vvvvvvvvvvvvvvvery much ? but i ask u one question? this card sharing working for dstv?
It works for all. | |
|
| |
dani.yohannes
Posts : 1 Points : 1 Reputation : 0 Join date : 2015-08-17
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Mon Aug 17, 2015 3:55 pm | |
| | |
|
| |
Kaleab470 Member
Posts : 102 Points : 119 Reputation : 11 Join date : 2015-06-21
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Mon Aug 17, 2015 11:59 pm | |
| My uncle has a Dstv and i was wondering if i can share it with him on my sm2350 powertech | |
|
| |
hageregenet
Posts : 3 Points : 3 Reputation : 0 Join date : 2015-07-30
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Tue Aug 18, 2015 12:49 am | |
| | |
|
| |
Admin Admin
Posts : 725 Points : 1175 Reputation : 303 Join date : 2014-09-01
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Tue Aug 18, 2015 10:16 am | |
| - Kaleab470 wrote:
- My uncle has a Dstv and i was wondering if i can share it with him on my sm2350 powertech
No, you can't. Because DSTV use pairing system. So you need DSTV receiver. | |
|
| |
Kaleab470 Member
Posts : 102 Points : 119 Reputation : 11 Join date : 2015-06-21
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Tue Aug 18, 2015 10:26 am | |
| We have unused dstv receiver at home with no card. Will that work? | |
|
| |
Admin Admin
Posts : 725 Points : 1175 Reputation : 303 Join date : 2014-09-01
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Tue Aug 18, 2015 10:41 am | |
| - Kaleab470 wrote:
- We have unused dstv receiver at home with no card. Will that work?
hopefully yes. Try it. | |
|
| |
Kaleab470 Member
Posts : 102 Points : 119 Reputation : 11 Join date : 2015-06-21
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Tue Aug 18, 2015 10:43 am | |
| What do i have to do first | |
|
| |
yordiyo
Posts : 3 Points : 3 Reputation : 0 Join date : 2015-09-03 Age : 31
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Mon Sep 07, 2015 7:44 pm | |
| | |
|
| |
yordiyo
Posts : 3 Points : 3 Reputation : 0 Join date : 2015-09-03 Age : 31
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Mon Sep 07, 2015 7:46 pm | |
| | |
|
| |
kibrulaw
Posts : 9 Points : 16 Reputation : 3 Join date : 2015-08-10
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Tue Sep 15, 2015 11:12 pm | |
| Message body... please....since card sharing is sophisticated....enlite us via video..pls | |
|
| |
yosef99 Junior member
Posts : 18 Points : 20 Reputation : 2 Join date : 2015-05-24 Age : 28
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Sat Sep 19, 2015 8:47 pm | |
| Do I box 3030 support sssp protocol | |
|
| |
Girma Zewdie
Posts : 1 Points : 1 Reputation : 0 Join date : 2015-09-22
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Tue Sep 22, 2015 4:43 pm | |
| I have got a very nice information. Thank you very much for your simplified explanation of the sophisticated technology. | |
|
| |
Admin Admin
Posts : 725 Points : 1175 Reputation : 303 Join date : 2014-09-01
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Tue Sep 22, 2015 4:54 pm | |
| - yosef99 wrote:
- Do I box 3030 support sssp protocol
No. That is one of the shortcoming of Ibox 3030. | |
|
| |
adisu yohanes
Posts : 9 Points : 12 Reputation : -1 Join date : 2015-03-07
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Sun Oct 04, 2015 2:44 pm | |
| አንዴት ኢንተሮኔት አንጠቀም ስለዚህም በደንብ ንገሩን | |
|
| |
onewow
Posts : 5 Points : 17 Reputation : 4 Join date : 2015-03-11
| Subject: 10 q u Wed Oct 14, 2015 1:28 pm | |
| | |
|
| |
biruk man123
Posts : 4 Points : 4 Reputation : 0 Join date : 2015-12-28
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV Fri Jan 01, 2016 1:41 pm | |
| ene yalegn ibox 3030 new endet cardsharing metekem endemechil step by step negeregn......
| |
|
| |
Sponsored content
| Subject: Re: Card sharing, Server, IPTV, Internet TV | |
| |
|
| |
| Card sharing, Server, IPTV, Internet TV | |
|